ከልብ ሲዋደዱ
ደስ ይላል መንገዱ
ተውቦ ባበቦች
ደምቆ በኮከቦች
ታጅቦ በቀልዶች
በሳቅ በጫወታ
በሚስብ ፈገግታ
በሚጥሙ ቃላት
በሚያምሩ ቀለማት
ከልብ ሲዋደዱ
በፍቅር ሲያብዱ
ምስጢር አይቋጥሩ
ተማምነው ይኖሩ
ጥል እንኳ ቢፈጠር
ውሎ የማያድር
ሆድ ውስጥ የማይጠጥር
ረምጦ የማያሳር
በይቅር ይቅርታ
ሳይከር የሚፈታ
የግልጽነት ጉዞ
ነገር ሳይሆን አዞ
የሚባላ አራዊት
ሳይታሰብ ድንገት
ከልብ ሲዋደዱ
ምቹ ነው መንገዱ
ጎርባጣ እንኳ ቢሆን
አያስመር አያስመንን
No comments:
Post a Comment