![]() |
፩ ዕርሳስ ለ ፩ ተማሪ !!!!!!
ይህ ፕሮግራም ከዛሬ 16 / ሐምሌ / 2006 እስከ 2 / ጳጉሜ /2006 የሚቆይ ይሆናል
አላማ:
የዚህ ፕሮግራም አላማ እርሳሶችን
በማሰባሰብ በመማሪያ መሳሪያ እጦት የተቸገሩ ታናናሸ እህትና ወንድሞቻችንን ተማሪዎች በተቻለ መጠን ማዳረስ ነው
ባሁን ሰአት ባብዛኛዉ አዲስ
አበባ ትምህርት ቤቶች (የመንግስት) ትናንሸ ሕፃናት በመማሪያ መሳሪያዎች እጦት ከትምህርት ገበታቸው ሲቀሩ እናያለን እንሰማለን ስለዚህም የኢትዮ-አማካሪ አባላት ይህንን ፕሮግራም አዘጋጅተናል
ለብዙሀኖቻችን እርሳስ ተራ ነገር
ሊመስለን ይችላል ነገር ግን ለታናናሸ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን እርሳስ መሰረታዊ የትምህርት መሳሪያ ነው ይህን መሳሪያ አተው
ከትምህርት ገበታቸው ሲቀሩ ማየት ደሞ በጣም ያማል ስለዚህም ፩ ዕርሳስ ለ፩ ተማሪ እናበርክት
አሰራር:
እርሳሶችን መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያችን ያሉ የመማሪያ መሳሪያ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች/ትምህርት
ቤቶችን አብረን በመጠቆም እርሳሶችን ማዳረስ ነው
ከርሳሶች ዉጪም ደፍተር ፤ እስክቢርቶ
እና የመሳሰሉትን ቁሳቁስ በማሰባሰብ በ2007 በአቅማችን የተወሰኑ ተማሪዎችን ፍላጎት እናሙዋላ ::
እምንችለዉን በማረግ የማይችሉትን እናግዝ !!!!
በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ የፈለገ በኢሜል አድራሻ ethioamakari@gmail.com ወይም በ facebook.com/pages/Ethioamakari-አማካሪ
መመካከር እንችላለን::
https://www.ethioAmakar/campaign1 |
Monday, July 28, 2014
፩ ዕርሳስ ለ ፩ ተማሪ [ እምንችለዉን በማረግ የማይችሉትን እናግዝ ! ]
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment