Sunday, June 15, 2014

ሰሞኑን የዶ/ር ኢ/ር ሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ አነጋጋሪ ኾኖ ሰንብትዋል



ሰሞኑን   የዶ/ / ሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ አነጋጋሪ ኾኖ ሰንብትዋል

በቅርቡ በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ “የትኛውም የሥራ ፈጠራ የሚመነጨው ከችግር ነው” በሚል ርዕስ ስር ስለሒወት ታሪካቸው የተጻፈውን አንብቤ ነበር በጣም አስገራሚና በእውነት ሰው እንዴት በዚ ሁሉ ነገር ውስጥ አልፎ

ትልቅ ደረጃ ላይ ይደርሳል ያስብላል፡፡ በዚህም ተገርሜ አድናቆቴን በልቤ ቸሬያቸው ነበር፡፡ለሚቀርቡኝ ጉዋደኞቼም ያነበብኩትን እንዲያነቡ አካፍያቸዉ ነበር ፡፡ ይሁንና ብዙም ሳልቆይ ዶ/ / ሳሙኤል ዘሚካኤል

ሐሰተኛ እንደሆኑ በሳምንቱ አንዱቀን ጠዋት በ ሬድዮ የማለዳ ዜና ላይ ዐደመጥኩ በጣም አሳዛኝ እና አስደንጋጭ ዜና ነበር፡፡

 

እናም ካነበብኩዋቸው ግጥሞች መካከል ከዚህ ጉዳይ ጋር ተስማሚ ይሆናል ስሜትን ይገለጻል ብዪ በማሰብ እንድታነቡት ይህን ግጥም ጋበዣለሁ፡፡




ሰው ፈልጉ
ለዕምነቱ ያደረ ቃሉነ የማይበላ
ፊትን ተመልክቶ ሰዉ የማያዳላ
እውነት ተናጋሪ የሚኖር ለነፍሱ
ለሰው የሚራራ አብልጦ ከራሱ
ፊት ለፊት አድንቆ ዞሮ የማያማ
በተንኮል በሃሜት ልብ የማያደማ
ጥሩ ወዳጅ መስሎ እየሸነገለ
ወንድሙን ለነዋይ ዋሽቶ ያልገደለ
አደራ ጠባቂ ምሎ የማይከዳ
እስኪ ሰው ፈልጉ ከሁሉ የፀዳ

No comments:

Post a Comment